loading
በደቡብ ኮሪያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡

በደቡብ ኮሪያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡

በትራንስፎርመር አማካይነት የተፈጠረው እሳት ጋንጉን በተባለች ግዛት ከ525 ሄክታር ባላይ መሬት የሚሸፍን ጉዳት አድርሷ ነው የተባለው፡፡

የአካባቢው የእሳት አደጋ ተቋም ሃላፊ ቾይ ጂን ሆ እሳቱ ከተቀሰቀሰበት ወደ ሌላ አካባቢዎች በፍጥን ተሰራጭቶ ነበር ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው 198 መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎችም የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው ለመፈናቀል ተገደዋል፡፡

አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የሚገኙ ከ52 በላይ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ መደረጋቸውንም ዘገባው አክሎ አመልክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የውህደት ሚንስቴር የእሳት አደጋው የተፈጠረው በሰሜን ኮሪያ ድንበር  አቅራቢያ በመሆኑ ጥንቃቄ እንድታደርግ ለጎረቤት ፒዮንግያንግ ሁኔታውን እናሳውቃለን ብሏል፡፡

ከ3 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በ 872 ተሸከርካሪዎች በመታገዝ ባደረጉት ርብርብ በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሳውን እሳት እስከ 50 በመቶ ድረስ መቆጣጠር መቻላቸው ተነግሯል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ አደጋውን ለመከላከል 16 ሺህ 500 ወታደሮችን፣ 32 ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን እና 26 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችን በቦታው አሰማርቷል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አንድ ሰው ህይዎቱ ማለፉ የታወቀ ሲሆን ሌሎች ዝርዝር ጉዳቶች ይፋ አልሆኑም፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *