loading
በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ግዛት የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት አለፈ

አርትስ 25/12/2010
በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ግዛት ውስጥ የሌላ አገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ኢትዮጰያውያን ራሳቸውን እንዲጠብቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ ፡፡
በእስከአሁኑ ጥቃት አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ሲያልፍ አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ሃኪም ቤት እያገገመ ይገኛል ብሏል የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ፡፡
ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከአገሪቱ መንግስት ጋር በመሆን በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቆም እየሰራ ይገኛል ብሏል ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየጠየቀ በፕሪቶሪያ ከሚገኘው ኤምባሲ መረጃ ለሚፈልጉ ሁሉ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች መደወል የምትችሉ መሆኑን አስታውቋል፡፡
0123462110
0123462947

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *