loading
በዩሮ 2020 የማጣሪያ ጨዋታዎች እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ፖርቱጋል ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

በበርካታ የአውሮፓ ስታዲየሞች ለሚካሄደው የዩሮ 2020 ውድድር ተካፋይ ለመሆን፤ የምድብ ሁለተኛ የማጣሪያ ግጥሚያዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል፡፡

ትናንት ምሽት ምድብ C ላይ ጀርመንን አምስተርዳም ላይ ያስተናገደችው ኔዘርላንድስ የ3 ለ 2 ሽንፈት ገጥሟታል፡፡ ከምድቡ ሰሜን አየርላንድ ቤላሩስን 2 ለ 1 በመርታት ምድቡን በስድስት ነጥብ መምራት ጀምሯል፡፡

በሪያን ጊግስ የምትሰለጥነው ዌልስ ምድብ E ላይ ስሎቫኪያ 1 ለ 0 ስታሸንፍ፤ ሀንጋሪ ክሮሽያን 2 ለ 1 ድል በማድረግ ገራሚ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

በምደብ G የሮበርት ሉዋንዶውስኪዋ ፖላንድ ሜዳዋ ላይ ላቲቪያን 2 ለ 0 ስታሸንፍ፤ እስራኤል በኦስትሪያ ላይ የ4 ለ 2 ድል ተቀዳጅታለች፤ ስሎቬኒያ ከ ሜቄዶኒያ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በምድብ I ቤልጂየም ቆጵሮስን በሃዛርድ እና ባትሹዬ ግቦች 2 ለ 0፤ እንዲሁም ስኮትላንድ ሳን ማሪኖን በተመሳሳይ ውጤት ሲረቱ ሩሲያ ካዛኪስታንን 4 ለ 0 ረምርማለች፡፡

ዛሬ ምሽት በርካታ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

ቀዳሚው ምድብ A ላይ በጋሪዝ ሳውዝጌት የምትመራው እንግሊዝ ወደ ደቡብ ምስራቅ አውሮፓ ተጉዛ በአመፅ ላይ የምትገኘውን ሞንቴኔግሮ ምሽት 4፡45 ላይ ትገጥማች፡፡ ኮሶቮ ደግሞ ቡልጋሪያን ከምድቡ ታስተናግዳለች፡፡

የማጣሪያ ውድደሯን በአቻ ውጤት የጀመረችው ፖርቱጋል እስታዲዮ ዳ ሉዝ ላይ ሰርቢያን ታስተናግዳለች፡፡

በአንድሬ ሼቪሼንኮ የምትሰለጥነው ዩክሬን ከሉክሰምበርግ ጋር ትፋለማለች፡፡

የዓለም ዋንጫው አሸናፊ ፈረንሳይ በስታዴ ደ ፍራንስ አይስላንድን ትገጥማለች፡፡

በምድቡ ቱርክ ከ ሞልዶቫ እና አንዶራ ከአልባኒያ ይገናኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *