በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ አርሰናል ከ ናፖሊ ተገናኝቷል፡፡
የዬሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች የዕጣ ድልድል ኒዮን ላይ ወጥቷል፡፡
የእንግሊዙ አርሰናል በሩብ ፍፃሜው ከጣሊያኑ ናፖሊ ጋር ተፋጥጧል፡፡ አርሰናል የመጀመሪያውን ግጥሚያ ሜዳው ላይ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ደግሞ ከቼክ ሪፐብሊኩ ስላቪያ ፕራሃ ጋር ተገናኝቷል፡፡
ሁለቱ የስፔን ክለቦች ቪያሪያል እና ቫሌንሲያ በሩብ ፍፃሜው ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል፡፡
የፖርቱጋሉ ቤንፊካ ከ አይንትራክት ፍራንክፉርት ጋር ይጫወታል፡፡
በግማሽ ፍፃሜው የአርሰናል እና ናፖሊ አሸናፊ ከ ቪያሪያል እና ቫሌንሲያ የሚገናኙ ሲሆን የቤንፊካ እና አይንትራክት ፍራንክፉርት ባለድል ደግ ከቼልሲ እና ስላቪያ ፕራሃ ጋር ይጫወታሉ፡፡
የዩሮፓ ሊጉ የመጀመሪያ ፍልሚያ መጋቢት 3/2011 ሲደረግ የመልሱ ጨዋታ መጋቢት 24/2011ይደረጋል፡፡