loading
በየመን የእርስ በእርስ ግጭት  ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ህጻናት ተገለዋል ተባለ፡፡

በየመን የእርስ በእርስ ግጭት  ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ህጻናት ተገለዋል ተባለ፡፡

በ2015  በየመን ከተከሰተዉና እስካሁን በዘለቀዉ የእርስበርስ ግጭት ምክንያት የሞቱት ህጻናት ከ6ሺህ 700 በላይ መሆናቸዉን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስቸኳይ የህጻናት ድጋፍ ፈንድ ዩኒሴፍ አስታዉቋል፡፡

ሚዲል ኢስት ሞኒተር የዬኒሴፍን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበዉ በግጭቱ ህይወታቸዉ ካለፉት ህጻናት በተጨማሪ 358 ሺህ ህጻናት  በምግብ እጦት እየተሰቃዩ በመሆኑ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ና የህክምና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል፡

በጎ አድራጊ ድርጅቶችና መንግስታት ለየመን ህጻናት በአስቸኳይ እንዲደርሱ ዩኒሴፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በየመን ግጭቱ በ2015 የተቀሰቀሰ ሲሆን ሳኡዲ አረቢያ መራሹ ጦር በየመን የመሸገዉን የሁቲ ሚሊሻ ጦር ለመዉጋት በሚል ነበር ጦርነቱን የተጀመረዉ፡፡

ከሳዉዳረቢያ ጎንም በመቆም አሜሪካና የተባበሩት አረብ  ኤምሬቶች በየመን ተደጋጋሚ ድብደባ አድርገዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሁዴዳ ወደብ ሁለት ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈራረሙ ቢያደርግም አስካሁን ተግባራዊ ስላልሆን ለየመን ህዝቦች አጠቃላይ መስረታዊ ሽቀጦችና መድሀኒቶች እንዳይገቡላቸዉ እንቅፋት ተፈጥሮባቸዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *