በዛምቢያ የ9ኛ ክፍል ፈተና መሰረቅ ጉዳይ ፓርላማ ድረስ አነጋግሯል
አርትስ 14/02/2011
የዛምቢያ ትምህርት ሚኒስቴር የ9ኛ ክፍል ፈተና በመሰረቁ ምክንያት ጉዳዩን ለሃገሪቱ ፓርላማ ግልጽ አድርጊያለሁ ብሏል፡፡
የሀገሪቱ የመረጃ ሚኒሰቴርና የመንግስት ቃል አቀባይ ዶራ ሶሊያ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከሆነ የ9ኛ ክፍል ሂሳብ ትምህርት ተሰርቆ በማህበራዊ ሚዲያ ጭምር መሰራጨቱን ደርሰንበታል ብለዋል፡፡
አክለውም ፈተናው እንዴት ሊሰረቅና ሊሰራጭ እንደቻለ እንደርስበታለን ፣ የማጣራት ስራዎችንም መስራት ጀምረናል ብለዋል፡፡ ተሰረቀ የተባለው የትምህርት አይነት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንም ተናግረዋል፡፡
ከሃገሪቱ ሚዲያዎች እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ፈተናው በማህበራዊ ድረ ገፅ መለቀቁ ቢወራም መንግስት ግን ችላ ብሎታል፡፡
ኒውስ 24 ከዛምቢያ እንደዘገበው ሌሎች ፈተናዎችም ይሰረቃሉ በሚል ስጋት በሃገሪቱ የ12 ኛና የ 7ኛ ክፍል ፈተናዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘሙ ተደርጓል