loading
በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡

በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 በተለያዮ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም ከሚሲዮኖች ሰራተኞች ከ100 ሚሊዮን ብር  በላይ መሰብሰቡን የብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታዉቋል፡፡ድጋፉ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በውጭ በሚገኙ 60 ሚሲዮኖች መሰባሰቡ ተጠቁሟል፡፡ ድጋፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ተረክበዋል።ሚኒስትሩ በዚህ  ወቅት ድጋፉ አገር በችግር ውስጥ ባለችበት ጊዜ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት በመሆኑ አመስግነዋል። በተለይ ራሳቸው ችግር ውስጥ ሆነው አገራቸውን እየረዱ ያሉ ወገኖች እንዲሁም ሚሲዮኖች እያደረጉ  ላለው  ድጋፍ  አድናቆታቸውን ገልጸዋል።በሀገር ዉስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ይሁን በዉጪ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን  ቫይረሱን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት ላይ ያላሳለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ጥረታቸዉን እደሚቀጥሉ ያላቸዉን ተስፋ ገልፀዉ በሽታዉ በሰው  ሕይወት ላይ እያደረሰ ያለው ችግር ትምህርት  በመውሰድ እያሳየ ያለውን መዘናጋት እንዲያስወግድ ጠይቀዋል።

የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የውጭ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው ድጋፉ በገንዘብ፣ በዓይነትና በዕውቀት መገለጹን አመልክተው፤በቀጣይም ድጋፋቸው ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።ድጋፉ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና ከእስያ አገሮች የተሰባሰበ ሲሆን፤በአውስትራሊያ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም መሳተፏ አምባሳደር ብርቱካን አስታውቀዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊና የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ የሚዲያ ንዑስ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት ድጋፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵውያን ወገንተኝነታቸውን ማሳያ ነው።ችግሩ ገና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል። ኅብረተሰቡም ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ እያሳየ ካለውን መዘናጋት እንዲወጣ አቶ ንጉሱ ጠይቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *