በወላጅ እናቱ ላይ ዛቻ የፈጸመው ተከሳሽ በ1 አመት ከ6 ወር እስራት ተቀጣ፡፡
በወላጅ እናቱ ላይ ዛቻ የፈጸመው ተከሳሽ በ1 አመት ከ6 ወር እስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ዳንኤል ተመስገን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታዉ ቀመጤ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሲሆን በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 590/1/ሐ ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ ድንጋጤን ወይም ፍርሀትን በሚቀሰቅስ ሁኔታ እናቱ የሆኑትን የግል ተበዳይ ወ/ሮ ወሰኔን ቢላዋ ይዞ እወጋሻለሁ በማለት ሲያሯሩጣቸዉ 2ተኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር ደርሶ ያስጣላቸዉ በመሆኑ በፈፀመዉ ከባድ የዛቻ ወንጀል ተከሷል፡፡
ተከሳሽ የወንጀል ዝርዝሩን ሲያስረዳ “ፈጽመሀል የተባልኩትን ድርጊት አልፈፀምኩም በዚህም ጥፋተኛ አይደለሁም” ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ቢሰጥም አቃቤ ህግ ድርጊቱን መፈፀሙን ያረጋግጡልኛል ያላቸዉን የሰዉ ምስክሮች አቅርቦ ለፍርድ ቤቱ አስደምጧል፡፡
ምስክሮቹን ያደመጠዉ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ 6ተኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽን ወንጀለኛ ነዉ በማለት በ1 አመት ከ6 ወር በእስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡