loading
በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዛሬ ጅማ አባ ጅፋር የሞሮኮውን ሀሳኒያ አጋዲር ያስተናግዳል

በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዛሬ ጅማ አባ ጅፋር የሞሮኮውን ሀሳኒያ አጋዲር ያስተናግዳል
2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመቀላቀል የደርሶ መልስ መጀመሪያ ግጥሚያዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
በአል አህሊ ከካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የተሰናበተው ጅማ አባ ጅፋር ወደ ኮንፌዴሬሽኑ ዝቅ ብሎ ወደ ምድብ ድልድሉ ደረጃ ለማሻገር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሞሮኮው ቡድን ሀሳኒያ ዩኒዮን ስፖርት አጋዲር ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 10፡00 ሲል ይጫወታል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ውድድሮች እየተካፈለ የሚገኘው የጅማው ቡድን፤ እንደ መጀመሪያ ተሳትፎው መልካም ጅምር የሚባል ነው፤ ተጋጣሚው ሀሳኒያ አጋዲር በካፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፎው ከጅማ አባ ጅፋር የተሻለ ቢሆንም በርከት ያለ አይደለም፡፡
ክለቡ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ በ2003 እና 2004 እስከ ሁለተኛ ዙር እንዲሁም በ2007 በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እስከ ሁለተኛው ዙር እንደተጓዘ የታሪክ ማህደሩ ያሳያል፡፡
በ1946 በሞሮኮዋ አጋዲር ከተማ የተመሰረተው ቡድኑ በ2017/18 በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሊግ ውድድር (ቡቶላ) ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡ በቅፅል ስማቸው ጋዜሌ ዴ ሱሴ ይሰኛሉ፡፡ ቡድኑን በአሰልጣኝነት አርጀንቲናዊው ሚጌል አንሄል ጋሞንዲ ይመሩታል፡፡

የዛሬውን ጨዋታ ማሊያውያን ዳኞች ሲመሩት፤ የመሃል አርቢትሩ ቦቡ ትራኦሬ ይሰኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *