loading
በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።ከዚህ ቀደም በቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ ባለሀብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች በኮቪድ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው ከዘርፉ በመውጣት ላይ ይገኛሉ በዚህም ምክንያት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እና ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ የተራራ ላይ ቱሪዝም ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ለተራራ ላይ ጉብኝት ምቹ መልክአ ምድር ቢኖራትም በዘርፉ በቂ የማስተወወቅ ስራ አለመሰራቱን ይነገራል።በኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 በላይ የሚሆኑ ተራሮች በ4ሺ የባህር ጠለል ከፍታ ላይ ይገኛሉ ። እነዚህ ተራሮች በሚፈለገው መጠን ከቱሪዝም ዘርፍ ከሚገኝ ገቢ ሀገሪቱ ተጠቃሚ ሳትሆን ቀርታለች።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ግራማ ይህንን የተፈጥሮ ስጦታ ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን በማስታወስ ለቱሪዝም ጥቅም ላይ ያልዋሉ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የ30 ኪ.ሜ የተራራ ላይ የብስክሌት ውድድር መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።ምንም እንኳን በሀገራችን የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ በኮረና ምክንያት ላለፉት አስር ወራት የተዳከመ ቢሆንም በሀረር፤በአክሱም፤በላሊበላ፤በባሌ፤በጂንካ እና በአርባ ምንጭ ተዘግቶ የነበረው የቱሪዝም መስዕቦች ተከፍተው አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት እንደገና ለማስጀመር በማሰብ ከዚህ ቀደም በትኩረት ያልተሰራባቸው ልዩ የሆነ መልከዓ ምድር ያላቸው ከአፋር ስምጥ ሸለቆ አዋሽ እስከ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት የሆነው ሰሜን ሸዋ አንኮበር ድረስ የባይ ኪንግ ቱር /የብስክሌት ጉብኝት/ ይካሄዳል ተብሏል።በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ቢታወቅም በኮቪድ ምክንያት የተዳከመውን ቱሪዝም ለማነቃቃት ፋይዳው ከፍተኛ ነው ተብሏል

በሀገሪቱ በአንፃራዊነት የተሻለ ሰላም አላቸው ተብሎ በታሰበባቸው ሁለት ክልሎች ውድድሩን ለማካሔድ መመረጣቸውን ቱሪዝም ኢትይጵያ አስታውቋል::በማውንቴን ቱር ከሚገኘው ገቢ በኮሮና ምክንያት የተጎዱ በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ወገኖችን ለመርዳት እንደሚውል የቱሪዝም ኢትይጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ግራማ ተናግረዋል።

በውድድሩም ከ 10 ሀገራት የተውጣጡ 60 ተወዳዳሪዎች ፤በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ፤ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች እንደሚሳተፉ ታውቃልውድድሩን በማዘጋጀት ከቱሪዝም ኢትዮጵያ በተጨማሪ አራት የሚሆኑ የግል የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።  ቴዎድሮስ ወርቁ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *