በኮምቦልቻ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ
አርትስ ታህሳስ 12 2011
በትናንትናው ዕለት በኮምቦልቻ ከተማ በተለምዶ ማርያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባትሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
አደጋው የቀን ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የጭነት አይሱዙ መኪና በመገልበጡ የተከሰተ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል ።
አደጋው ምሽት አንድ ሰዓት ላይ የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የኮምቦልቻ ከተማ የመንገድ ደህንነት የስራ ሂደት ባለቤትምክትል ኮማንደር ወሰን አሰፋ በአደጋው የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።
ተሸከርካሪው በአጠቃላይ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ እንደነበርም ምክትል ኮማንደሩ ጠቅሰዋል።