loading
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዮ ስሙ ብርጭቆ ኮንደሚኒየም የሚገኙ ባለሀብት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት አካሄዱ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዮ ስሙ ብርጭቆ ኮንደሚኒየም የሚገኙ ባለሀብት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት አካሄዱ ፡፡
ግለሰቡ 10 ሺ አባወራዎች በሚገኙበት አካባቢ ኬሚካል ያስረጩ ሲሆን በዚህ ወቅት የራስን ጤንነት ብቻ ሳይሆን የአካባቢንና የህብረተሰብን ጤና ማስጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ኬሚካሉ የማህበረሰቡን ፍቃደኝነት በመጠየቅ እቤት ለቤት በመዘዋወር የተረጨ መሆኑን በዚህ ፈታኝ ጊዜ ሁሉም የሚችለዉን በማዋጣት መረዳዳት አስፈላጊ እንደሆነ ባለሀብቱ ኢ/ር መኩሪያ በየነ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም በዚህ ወቅት ስንረዳዳ አካላዊ ርቀታች የተጠበቀ ቢሆንም በይበልጥ ግን መረዳዳት ማህበራዊ መስተጋብራችንን ከመጠናከሩም ባሻገር ለሂሊናችን እፉይታን የሚፈጥርልን ነዉ ብለዋል፡፡የአካባቢዉ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ በየትኛዉም ሀይማኖት የመረዳዳት ባህልን የሚደግፍ በመሆኑ ሌሎችም ባለሀብቶች ያላቸዉን በማካፈልና ኢ/ር መኩሪያ በየነን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ በሚችሉት ድጋፍ እንዲያደርጉ የጠየቁ ሲሆን ባለሀብቱ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ከባሀብቶች በተጨማሪ የተለያዮ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሙያተኞችና ሁሉም ህብረተሰብ ለሀገር በመቆም እንዲረባረብም ጠይቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *