loading
በካራባዎ ዋንጫ ቶተንሃም ቼልሲን ድል አድርጓል

በካራባዎ ዋንጫ ቶተንሃም ቼልሲን ድል አድርጓል

የካራባዎ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ትናንት ምሽት በዊምብሌይ ተካሂዷል፤ በቶተንሃም ሆትስፐርና ቼልሲ መካከል በተደረገው የለንደን ደርቢ ጨዋታ የሰሜን ለንደኑ ቡድን የ1 ለ 0 ድል አግኝቷል፡፡

የስፐርሶችን የድል ግብ አጥቂው ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት በመጀመሪያው አጋማሽ 26ኛ ደቂቃ ላይ ያስቆጠረ ሲሆን ፍፁም ቅጣት ምቱ የተሰጠበት መንገድም አጨቃጫቂ ነበር፡፡ የጨዋታው አርቢትር ማይክል ኦሊቨር ውሳኔ ለማሳለፍ የቫርን እገዛ ቢጠይቁም የፈጀው ጊዜ ግን አሁንም የቫር ተግባራዊነት ላይ ወፈራም ጥያቄ ምልክት እንዲቀመጥ አሳይቶ አልፏል፡፡ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ እና ሳሪ ቫርን በደንብ ተችተውታል፡፡

ኬን ከ25 ፍፁም ቅጣት ምቶች 21ን ወደ ግብነት መቀየር ችሏል፡፡

ቼልሲዎች በንጎሎ ካንቴ እና ካሉም ሁድሰን ኦዶይ አመካኝነት ግብ ለማስቆጠር ቢሞክሩም የግብ ብረቱ የስፐርሱ ግብ ጠባቂ ፓውሎ ጋዛኒጋ አጋር ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ግጥሚያ ከ15 ቀን በኋላ በስታንፎርድ ብሪጅ ይካሄዳል፡፡

ዛሬ ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ፍልሚያ ኢቲሃድ ላይ በማንችስተር ሲቲና በርተን አልቢዮን መካከል ምሽት 4፡45 ይካሄዳል፡፡

የባለፈው ዓመት የካራባዎ ዋንጫ ባለድል ሲቲ በኩል አዲስ ጉዳት እንደሌለ የተነገረ ሲሆን ፔፕ ጓርዲዮላ ማሸነፍ በጣም አስፈላጊያችን ነው፤ ልንንቀውአይገባም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *