loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ  አሁንም ማሸነፉን ቀጥሏል፤ ዛሬ ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ  አሁንም ማሸነፉን ቀጥሏል፤ ዛሬ ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡

የ21ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ቀጥለው ተካሂደዋል፤ በምሽቱ ስድስት ያህል ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ በስታንፎርድ ብሪጅ የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ የደቡብ ጠረፉን ቡድን ሳውዛምፕተን አስተናግዶ ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡

በጨዋታው 72 በመቶ የጨዋታ ቁጥጥር የነበራቸው ሰማያዊዎቹ፤ ወደ ግብ ግን መቀየር አልቻሉም፡፡ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ሳሪም ከቀናት በፊት ከአጥቂ ይልቅ የክንፍ መስመር ተጫዋች ማስፈረም ነው የምፈልገው ቢሉም የቡድናቸውን ክፍተት በትናንቱ ጨዋታ በደንብ ተመልክተውታል፡፡

ከጨዋታው በኋላ በሜዳው 80 ሜትሮች ያህል ጥሩ ጨዋታ አድርገናል፤ ችግራችን ግን በቀጣዮቹ 20 ሜትች ላይ ይፈጠራሉ ብለዋል፡፡ ይሄንንም ችግር ለመቅረፍ እንተጋለን ሲሉ

አልቫሮ ሞራታን የታወቀ አጥቂያቸው አድርገው የሚቆጥሩት ሳሪ በጨዋታው ምንም ያልፌደላቸው ሲሆን አልፎ አልፎ የሚሰለፈውም ኦሎቪዬ ጅሩ ቢሆን በጉዳት አልተገለገሉበትም፡፡

በምሽቱ በዲን ኮርት በርንማውዝ ከ ዋትፎርድ ያደረጉት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ ስድስት ያህል ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን ጨዋታው በ3 ለ 3 አቻ ተጠናቋል፡፡ ትሮይ ደኒ ሁለትና ሴማ ለዋትፎርድ እንዲሁም አኬ፣ ዊልሰንና ፍሬዘር ለባለሜዳው በርንማውዝ አስቆጥረዋል፡፡

በኦሎምፒክ ስታዲየም በብራይተን የስቴፈንስና ዱፊ ግቦች 2 ለ 0 ሲመራ የነበረው ዌስት ሃም በአርናቶቪች ሁለት ጎሎች አቻ መሆን ችሏል፡፡  ወልቭስ በ ክሪስታል ፓላስ የ2 ለ 0 ሽንፈት ሲያስተናግድ፤ በርንሊ ሀደርስፊልድን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡

ኒውካስትል ዩናይትድ በሴንት ጀምስ ፓርክ ማንችስተር ዩናይትድ አስተናግዶ የ2 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ በጨዋታው ቀያይ ሰይጣኖቹ በማግቢሶች ቢፈተኑም ሶልሻየር ቡድኑን ከተረከበ በኋላ የሮሜሉ ሉካኩና ማርኮስ ራሽፎርድ ጎሎች ድል አራተኛ ተከታታይ ድል ነው፡፡

ዛሬ የ21ኛው ሳምንት መቋጫ ጨዋታ በኢቲሃድ ሲደረግ የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ የየርገን ክሎፑን ሊቨርፑል ምሽት 5፡00 ላይ ያስተናዳል፡፡ ሊቨርፑል ድል የሚቀናው ከሆነ ለሻምፒዮንነት የሚያሳጨው ይሆናል፤ በአንፃሩ ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያጠብበት ዕድል ይፈጠራል፡፡

በጨዋታው ባለሜዳው ሲቲ ከሳውዛምፕተኑ ግጥሚያ ውስጥ ያልነበረው ኢልካይ ጉንዶሃን የተመለሰ ሲሆን ኬቨን ዴ ብሯይኔም ወደ ልምምድ ተመልሷል ተብሏል፡፡ ፋቢያን ደልፍና ቤንጃሚን ሜንዲ በጉዳት ከዚህ ጨዋታ ውጭ ናቸው፡፡

በቀያቹ በኩል አማካዩ ጀምስ ሚልነር ከጉዳት የተመለሰ ቢሆንም የጆርዳን ሂንደርሰንና ናቢ ኬይታ ጉዳይ አልለየም፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ ሊቨርፑል በ54 ነጥብ ይመራል፤ ቶተንሃም በ48 ይከተላል፣ ማን. ሲቲ በ47 ሶስተኛ፣ ቼልሲ በ44 አራተኛ፣ እንዲሁም አርሰናልና ማን.ዩናይትድ በ41 እና 38 ነጥብ አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *