loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ::

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡

ትግራይ ስታዲየም ላይ በተደረገው ጨዋታ  አማኑኤል ብረሚካኤል ለባለሜዳዎቹ ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ አደረገ፤ እንግዳው ቡድን በማማዱ ሲዲቤ አቻ መሆን ቢችልም የትግራዩ ቡድን በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ በኦሴይ ማውሊ ግብ አሸናፊ ሁኗል፡፡

በገብረመድህን ሀይሌ የሚሰለጥነው ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ ዘጠነኛ ተከታታይ ድሉን ማሳካት ችሏል፡፡

በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ በ35 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል፤ ሲዳማ ቡና በ30 ነጥቦች ሁለተኛ ነው፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥብ ሶስተኛ፤ ፋሲል ከነማ በ25 አራተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በ22 ነጥቦች ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ምንይሉ ወንድሙ ከመከላከያ እና አማኑኤል ብረሚካኤል ከመቐለ በዕኩል 11 ጎሎች ሲመሩ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በ10 ይከተላቸዋል፡፡

የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይከናወናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *