loading
በኢትዮጵያ የዳያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው ፡፡

አርትስ 01/13/2010
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ኤጀንሲው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ እትዮጵያውያንን ጉዳዮች የሚያስተባብር የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤት ሆኖ ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ብሏል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንዳሉት መንግስት በውጭ ለሚገኙ የዳያስፖራ አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመምጣቱ የዜጎች አስተዋፅኦ ጨምሯል፡፡
በሃገሪቱ እየታየ ባለው የተሻለ የፖለቲካ ሁኔታ ዳያስፖራው በሃገሩ ጉዳይ የመሳተፍ ተነሳሽነቱ ጨምሯል ያሉት አቶ መለስ ለነዚህና መሰል እንቅስቃሴዎች አደረጃጀቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት በሃገር ውስጥ ብቻ ያልተወሰነ እነደሆነ እና መዋቅሩን እስከ ወረዳ ድረስ በማውረድ በየጊዜው የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ብለዋ ቃል አቀባዩ፡፡
በኤጀንሲው በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት የውጭ ሃገራት መብትና ክብራቸው እንዲጠበቅ ይሰራልም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *