በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት ቁጥር 46 ደረሰ፡፡
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት ቁጥር 46 ደረሰ፡፡የጤና ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀዉ የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ሲረጋገጥ ምንም ዓይነት የመመርመሪያ ማዕከል ያልነበራት ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት 46 ማዕከላት አላት ብሏል፡፡የጤና ሚኒስቴር ይህን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ በአገር ውስጥ የመመርመሪያ መሳሪዎችን በሟሟላት እና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የላብራቶሪ ምርመራ ማዕከላትን አደራጅቷል፡፡
የሚኒስቴሩ የመመርመር አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንደመጣም ገልጿል፡፡እስከ ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለ112,377 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተከናወነ ሲሆን ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ በአጭር ጊዜ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) በሽታ የላብራቶሪ ምርመራ አቅም እየጨመረ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡በቀጣይ የምርመራ ማዕከላትን የማስፋፋት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡