loading
በኢትዮጵያ የሚከበረው የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መረጃ ለህዝብ ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ነው ለ30ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው። ከ 30 አመት በፊት በናሚቢያ መከበር የጀመረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ መንግስታት የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብሩ መነሻ ሆኗል። በኢትዮጵያ የሚከበረውን አለምአቀፉ የፕሬስ ቀን በማስመልከት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በሀገራችን የፕሬ ነፃነትን ስናከብር ጋዜጠኞች ደህንነታቸው ተከብሮ ለስራው ትኩረት እንዲሰጡ ለማስቻል መሆኑን የመገናኛና ብዙሃን ምክር ቤት ካውንስል ሰብሳቢ ትዕግሥት ይልማ ገልፀዋል። በተለይም መጪውን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከሀሰተኛ መረጃና ከጥላቻ ንግግር የፀዳ እንዲሆን ባለሙያው ጥልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ዩኔስኮና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከፍድሪክ ኤበርት እስቲፍቶንግ ጋር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ባልደረባችን አቢ ፍቃዱ ከስፍራው ዘግባለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *