በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ
በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ
አርትስ 07/ 04 /2011
ሰሞኑን አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ኮሚሽነሩ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራሉ አገራችን ኢትዮጵያ የኢንተርፖል አባል ከሆነች ከ60 ዓመት በላይ እንደሆናት እና አሁን ከ194 ሃገራት ጋር ግንኙነት ያላት መሆኑን ገልጸው አሁን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠልና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ከሁሉም ሃገራት ጋር መልካም ግንኙነታችን ማጠንከር ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ከዋና ኃላፊው ጋር በነበራቸው ቆይታ በዋናነት በሁለት ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን 1ኛው የኢንተርፖል ስራዎችን በተድራጀ መልኩ ለመስራት በግብዓት፤ በስልጠናና የቴክኖለጂ እገዛን ሲመለከት 2ኛው የኢንተርፖል ደንብ በሚፈቅደው መሰረት በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የሚጠረጠሩትን የትም ሃገር ወንጀል ፈጽመው መደበቅ እንደማይችሉ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡
የኢንተርፖል ኃላፊው ዶክተር ጀርገን በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን የጀመረችውን የእደገት ጎዳና በማድነቅ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠትና የፎረሲክ ምርመራው በቴክኖለጂ የታገዘ እንዲሆን እና ማንኛውም ሰው ወንጀል ፈጽሞ የትም ሃገር መደበቅ እንደማይችል ተናግረዋል፡፡