በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ዉስጥ ከቀረጥ ነጻ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ አልዋለም ተባለ፡፡
በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ዉስጥ ከቀረጥ ነጻ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ አልዋለም ተባለ፡፡
ከ2002 እስከ 2010 ብቻ የአገሪቱ ገንዘብ ከከረጥ ነፃ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ አለመዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰራተኞቻቸዉ ጋር ባደረጉት ዉይይት
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም በሌብነት መረብ የተተበተበ፤ ለማጭበርበርና ታክስ መሰወር የሚያግዙና ዉስብስብ የሆኑ ህጎችና የስራ መመሪያዎች የነበሩበት፤ ወቅቱና ቦታዉ የሚፈልገዉ የሰዉ ሃይል በሚመጥነዉ ቦታ ያልተመደበበት፤ ከግዜ ወደ ግዜ ገቢዉ እያሽቆለቆለ የነበረበትና የንግዱ ማህበረሰብ የቅሬታ ቋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአገሪቱ የኮንትሮባንድ ዝዉዉር ከፍተኛ ሆኖ ሳለ 55 ኬላዎች ብቻ እንዲኖሩ መደረጉና ኬላዎቹም ያሉበት ስፍራ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ባለበት ቦታ አለመሆኑ መስሪያ ቤቱ የነበረበት ችግር መሆኑ ተነስቷል፡፡
ከሪፎርሙ ወዲህ ግን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያስፈልገዉ የሰዉ ሃይል በብቃትና በዉጤታመነት በመመደቡ በስራ ስኬት እየተመዘገበ ነዉ ተብሏል፡፡
ያለአግባብ ከቀረጥ ነፃ በሚል ከታለመለት አላማ ዉጪ እንዲዉል ሲደረግ ከነበሩት ስራዎች ዉስጥ በፍርድ ቤት በመክሰስ 1.5 ቢሊየን ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ መደረጉ ፤ከዉዝፍ እዳ 14 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉና ከአምናዉ ጋር ሲነፃፀር ሲያሽቆለቁል የነበረዉ ገቢ በ12በመቶ እድገት ማሳየቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሪፎርሙ እያመጣ ያለዉ ለዉጥ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑ ተነስቷል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አሰራር ቆልፈዉ የያዙና ለሌብነት በር የሚከፍቱ ከ34 በላይ ህጎች እየተሻሻሉ መሆናቸዉና 1.3 ቢሊየን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙ ህገወጥነት ሊቀጥል እንደማይችል ማሳያ መሆኑ በዉይይቱ ተነስቷል፡፡
መስፈርት ሳያሟሉ ለቦታዉ የሚያስፈልግ የትምህርትና የስራ ልምድ ሳይኖራቸዉ ከመከላከያ በየኬላዎች ተመድበዉ ይሰሩ የነበሩ 108 ሰዎች በአመራሩ ዉሳኔ እንዲነሱ ተደርጎ፤ በቂ የስራ ልምድና እዉቀት ባላቸዉ ሰዎች መተካታቸዉ፤ የኬላዎቹ ቁጥር ላይ 39 አዳዲስ ኬላዎችን በመጨመር 94 እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡