loading
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  55 ደረሰ፡፡

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  55 ደረሰ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2012 ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር 2 እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።ህብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ነው ያሳሰቡት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *