loading
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 ደረሰ

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ነዉ የጤና ሚኒስቴር የገለጸዉ፡፡የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።
ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
በኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ በስፋት ምርመራ ለማካሄድ እየተሰራ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *