loading
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ “ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የዳያስፖራ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የዳያስፖራ አባላቱ አሸባሪው ህወሃት በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳትና ውድመት ለመጎብኘት ነው ትናንት አመሻሽ ወደ ስፍራው ያቀኑት፡፡ የዳያስፖራ አባላቱ ሰመራ ከተማ ሲገቡ በክልሉ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በዛሬው ዕለት የምክክር መድረክ ጀምረዋል።

አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡ በምክክር መድረኩ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


በክልሉ በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች አሸባሪው ህወሃት ያደረሰውን ውድመትና ዘረፋ በተመለከተ በምስል የተደገፉ መረጃዎች በመድረኩ ላይ ቀርበዋል።
አሸባሪው ቡድን በክልሉ በወረራ በቆየባቸው 150 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በሚያስተናግዱ 750 ትምህርት ቤቶች ላይ ውድመትና ዘረፋ ስለመፈፀሙ በመድረኩ ላይ ተብራርቷል። ከምክክር መድረኩ በተጨማሪ የዳያስፖራ አባላቱ በክልሉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲጎበኙ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *