loading
በአዲስ አበባ የ3ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 ለቀጣዮቹ 10 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ክትባት ዕድሜያቸው12 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሁሉ አገልሎቱን እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡ ክትባቱ በሁሉም የመንግስት ጤና ጣቢያዎችና ሌሎች የተመረጡ ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

በዚህ የ3ኛው ዙር የክትባት ዘመቻም መጠኑ 249 ሺህ የሚሆን የክትባት ዶዝ ለመስጠት መታቀዱን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ኮቪድ 19 አሁንም በህብረተሰቡ ዘንድ የጤና ስጋት ሆኖ መቀጠሉና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ ሲሆን ይህን ጫና ለመቀነስ ክትባቱን መውሰድ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
የአዲስአበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ 3ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻውን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሚኪሊላንድ ጤና ጣቢያ ተገኝተው አስጀምርዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *