በአዲስ አበባ የመታወቂያ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡን አስተዳደሩ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሰጥ የቆየው የመታወቂያ አገልግሎት በጊዜያዊነት ላልተወሰነ ጊዜ
መቋረጡን የከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጄንሲ አስታዉቋል።
ኤጄንሲው ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የመታወቂያ መስጠት አገልግሎት
በጊዜያዊነት እንዲቆም የተወሰነው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንዲቻል
መሆኑን ገልጿል።
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በአስቸኳይ መታወቂያ ለሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎች አገልግሎቱን
የሚያገኙበት አሰራር መመቻቸቱንም የኤጀንሲው ዋና ዳይሪክተር ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ተናግሯል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጥ የሆነ በአሻራ የሚሰራ አዲስ መታወቂያ በሙከራ ላይ መሆኑን
ያስታወቀው ኤጀንሲው በአዲሱ መታወቂያ ላይ ብሄርን የሚጠይቅ ቦታ እንደሌለውም ተገልጿል፡፡