loading
በአዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ ጋር በመንግስት ትምህርት ቤቶች ሊሰጥ ነው

አርትስ 15/01/2011
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አፋን ኦሮሞን ከአማርኛ ጋር በመንግስት ትምህርት ቤቶች አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ ሊጠቀም ነው ተባለ
ይህ የተባለው የቢሮዉ ሃላፊ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን የ2011ዓመተ ምህረት የትምህርት አሰጣጥ እና ዝግጅትን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡
ኃላፊዉ እንዳሳወቁት በየደረጃዉ ያለዉ የትምህርት ማህበረሰብ ለትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራት፣ተገቢነት እና ፍትሃዊነት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀው አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር እንደየተማሪዉ የመማር ፍላጎት መጠን በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ እንደሚጠቀም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *