loading
በአዲስ አበባ ቡራዮ በተለምዶ አሸዋ ሜዳ በሚባል አካባቢ በተነሳ ግጭት የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደቀያቸው ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቋመ

አርትስ 06/01/2011
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማምሻውን እንደገለፁት በተለምዶ ቡራዩ እና አሸዋ ሜዳ ተብለው በሚጠሩት አካባቢዎች የሰው ህይወት አልፏል ። በዚህም የተነሳ በርካቶች ከመንደራቸው ተፈናቅለዋል። ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል ያሉ ሲሆን ከከተማው እና ከኦሮሚያ ክልል ኮሚቴ መቋቋሙን ገልፀዋል።
አርትስ በዚህ ሰዓት እንደተመለከተው ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ አንፃራዊ ሰላም ያለ ቢመስልም እንቅስቃሴው ወደ ቀድሞ ቦታው አልተመለሰም። ነዋሪዎቹም የፍትህ ጥያቄ እያቀረቡ ነው። ከንቲባው ጠዋት ላይ የተፈናቀሉ ወገኖችን በተጠለሉበት ተገኝተው የጎበኙ ሲሆን አሁንም አንዳንዶች በስጋት አካባቢያቸውን እየለቀቁ እንደሚገኙ ለአርትስ ተናግረዋል።
የትናንቱንድርጊት ሁሉንም ያሳዘነ ኢሰብአዊ ድርጊት ነው። ሲል የከተማ አስተዳደሩ አውግዟል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *