loading
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ባርሳ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ተገናኝተዋል

የ2017/18 የአውሮፓ ቻምፒንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል በሲውዘርላንድ ኒዮን ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም የድልድሉ ተጠባቂ ጨዋታ ወይንም ከባድ ፍልሚያ የተባለው በባርሴሎና እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያው ግጥሚያ ኦልድ ትራርድ ላይ ይደረጋል፡፡ ከወዲሁም የ2009 እና የ2011 የፍፃሜ ጨዋታ እየተወሳ ይገኛል፡፡

የባለፈው ዓመት የቻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ተፋላሚ ሊቨርፑል ከ ፖርቱጋሉ ፖርቶ ጋር ይገናኛል፡፡

ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች ቶተንሃም እና ማንችስተር ሲቲ ተገናኝተዋል፡፡

ሌላኛው ጨዋታ በአያክስ እና ዩቬንቱስ መካከል ይደረጋል፡፡

የባርሴሎና እና ማንችስተር ዩናይትድ አሸናፊ ከ ሊቨርፑል እና ፖርቶ አሸናፊ እንዲሁም የቶተንሃም እና ማ. ሲቲ አሸናፊ ደግሞ ከአያክስ እና ዩቬንቱስ ጋር በግማሽ ፍፃሜው ይፋጠጣል፡፡

የሩብ ፍፃሜው የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሚያዚያ 1 እና 2/2011 ሲከናወኑ፤ የመልሱ ደግሞ በሚያዚያ 22 እና 23/2011 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *