loading
በአንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጠረ ያለው አለመረጋጋት የቱሪዝም ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትላንት በመስሪያቤቱ በሰጠው መግለጫላይ ነው፡፤
በመግለጫው የቱሪዝም ዘርፍ ሰላም እና መረጋጋትን የሚሻ ዘርፍ እንደመሆኑ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተከሰቱት ግጭቶች ቱሪስቶችን እና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን ዲያስፖራዎችን የሚያሸሽ ነው ተብሏል፡፡
በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ድርጊት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንደሚያወግዘው ገልፀው ለሰላም እና መረጋጋት በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
ሚንስትሯ ባህላዊ እሴቶች ላይ ሚንስቴር መስሪያቤቱ ከዚህ ቀደም ከነበረው በይበልጥ ለመስራት ሪፎርም እና እቅድ የነደፈ ሲሆን በተለይ እንደ ገዳ እና የሽምግልና ስርዓት ያሉ ባህላዊ ግጭት መፍቻ መንገዶች ላይ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *