loading
በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኛች ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀመሩ፡፡

የፕሬዝዳን ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ባወጣው ህግ ሰነድ አልባ ስደተኞች በማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ ህጻናቱ ለብቻቸው እንዲኖሩ ተገደው ነበር፡፡
አሁን ግን የአሜሪካ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት እድሜያቸው ከ5-17 ያሉ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀምረዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው እስካሁን 1ሺህ 800 ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር የመቀላቀል ዕድል አግኝተዋል፡፡
2ሺህ 500 ህጻናት ወላጆቻቸው ህገ ወጥ ናችሁ ተብለው በስደተኞች ማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በብቸኝነት እንዲኖሩ ተፈርዶባቸው ነበር ይላል ዘገባው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *