loading
በአሜሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 30፣ 2013 በአሜሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱ ተሰማ፡፡ ከሶስት ወር ተኩል በኋላ በአሜሪካ በየቀኑ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በታች ሆኖ መመዝገቡን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ አድርጓል፡፡ ለአሜሪካዊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች 749 ብቻ መሆናቸው ከወራት በኋላ የተሰማ መልካም ዜና ሆኗል፡፡

ፍራንስ 24 እንደዘገበው 10 በመቶ ለሚሆነው ህዝባቸው ክባት እንዲዳረስ ላደረጉትና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ቆርጠው ለተነሱት ጆ ባይደን ለወሰዱት እምጃ የውጤት ማሳያ ጅምር እንደሆነም ተነግሯል፡፡ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች በትንሽ ቁጥር በቤት ውስጥ የግድ የፊት መሸፈኛ
ጭንብል ማድረግ ሳያስፈልጋቸው መገናኘት እደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ክትባቱን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር ሲገናኙና ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ ሲሆኑ የተለመዱትን የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል ግድ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ብለዋል ባለሞያዎቹ፡፡ አሜሪካ እስካሁን በቫይረሱ በተያዙና በሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን ከ29 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በበሽታው ተጠቅተው ከነዚህ መካከል ከ35 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው አልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *