በአልጀሪያ ውሀን ብቻ የሚጠብቅ የፖሊስ ሀይል መቋቋም አለበት እየተባለ ነው፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ሰሞኑን ውሀን በመበከል የህዝቡን ጤና አደጋ ላይ ጥለዋል ያላቸውን በርካታ ሰዎች ይዞ አስሯል፡፡
ግብጽ ውስጥ የሚታተመው ሾሩክ ጋዜጣ እንደዘገበው የተበከለ ውሀን አትክልት ለማጠጣት የተጠቀሙ እንዲሁም በውሀ ውስጥ ጤናን የሚጎዳ ውሁድ ጨምረዋል የተባሉ 1 ሺህ 744 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ የታሰሩትም ከፍሳሽ ማስወገጃ በተለቀቀ ውሀ አትክልቶቻቸውን ሲያጠጡ በመገኘታቸው ነው፡፡
በአልጀሪያ ብዙ ሰዎች በኮሌራና ሌሎች ከውሀ ጋር ግንኙነት ባላቸው ህመሞች እየተያዙ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የአልጀሪያ የአካባቢ ደህንነት ጥበቃና የውሃ ሀብት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውሀን ብቻ የሚጠብቁ ፖሊሶች መኖር አለባቸው እያለ ነው ፡፡
አርትስ 25/12/2010