በታንዛንያ እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው
በታንዛንያ ታንጋ በሚባል ከተማ በሚገኝ ማዌይኒ በሚባል እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅኅፈት ቤት አስታውቋል።
ስደተኞቹን ኢትዮጵያውያን የመመለሱን ስራ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ተብሏል።
ከ3 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ቦታ የነበሩ 50 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ። ቀሪዎቹ 235 ዜጎች ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት በ6 ዙር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል።
መንግስት ለዜጎች ዲፕሎማሲ በሰጠው ልዩ ትኩረት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከተለያዩ አገሮች እስር ቤት እየተለቀቁ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ።