loading
በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ማንነቷ ያልታወቀች ሴት ባደረሰችው ፍንዳታ 9 ሰዎች ተጎድተዋል

በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ማንነቷ ያልታወቀች ሴት ባደረሰችው ፍንዳታ 9 ሰዎች ተጎድተዋል

አርትስ 20/02/2011

 

የቱኒዚያ የሃገር ውሰጥ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ድርጊቱ የአሸባሪ ቢመስልም ሴትየዋ ግን የመከላከያም ሆነ የአሸባሪነት ታሪክም ሆነ ንክኪ  የላትም ፡፡

ፍንዳታውን በተመለከተ ክትትል እየተደረገ ቢሆንም፤እስካሁን በአደጋው የሞተ ሰው እንደሌለ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

እስካሁን ድረስ ድርጊቱን ፈፅሚያለው ብሎ ሃላፊነት የወሰደ አሸባሪ ድርጅትም ይሁን ሌላ ተቋም  የለም፡፡

ቢቢሲ ከቦታው በሪፖርተሩ አረጋገጥኩት እንዳለው ፍንዳታው ኢላማ ያደረገው  በአካባቢው የሚገኘውን የፖሊስ መቆጣጠሪያ ስፍራ ሳይሆን እንዳለቀረ ተናግሯል፡፡

በቱኒዚያ ከሶስት ዓመታት በፊት በተለያየ ጊዜ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች ደርሰው 60 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ መቀዛቀዙ ይነገራል፤የጎብኚዎች ቁጥርም አሽቆልቁሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *