loading
በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የአየር ወለድ አሰልጣኝ የነበረችው መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ተፈታች፡፡

ወደ መከላከያ ሠራዊት የተቀላቀለችው በ1997 ዓ.ም የሥልጠና ቦታው ብር ሸለቆ የምልምል ወታደሮች ማሠልጠኛ ነው፡፡ አይዳ በውትድርና ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ያመጣች ተመራቂ ናት፡፡ በፓራሹት 27 ጊዜ በመዝለል የምትታወቀው አይዳ በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በ2009ዓ.ም ስትሰለጥን ከ1800 ሰልጣኞች አንደኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡
በቅርቡ ከሽብር ቡድን ጋር ተገኛኝተሻል ተብላ ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡ በተጨማሪም ውስጥ ለውስጥ ሠራዊቱን በማነሳሳት አገር በማስከዳት ወደ ሽብር ቡድን በመግባት ስልጠናዎችን በመስጠት፣ በተቋሙ ውስጥ የነበሩትን መረጃዎች ለኦነግ እንዲሁም ለአርበኞች ግንቦት 7 በማስተላለፍ፣ ከቀድሞ የደርግ ሠራዊት ጋር በክፍሉ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች በመለዋወጥ፣ ኮብልለው ከሄዱ የአየር ኃይል አባላቶች ጋር እንደሚኮበልሉ እያወቀች መረጃ በመደበቅ፣ በ2006 ዓ.ም ወደ ሱማሌ የሰላም ማስከበር ግዳጅን አልቀበልም ብላለች በሚል ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡ አሁን ግን ተፈታለች፡፡
አርትስ ከመ/አለቃ አይዳ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ይጠብቁ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *