በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ የላከው መግለጫ እንደሚያስረዳው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በንፁሃን ዜጎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል እና የምእራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በቅንጅት በሰሩት ስራ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ እጅ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉ የጦር መሳሪያዎች መካከልም 2 ብሬይን፣ 27 ክላሽንኮቭ፣ 4 የእጅ ቦምብ፣ 5 ሽጉጥ እና 87 የተለያዩ ጥይቶች ይገኙበታል ነው የተባለው።