በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች ወሰኖች አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን በሠላም እንዲሰጡ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች ወሰኖች አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን በሠላም እንዲሰጡ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባው ኮማንድ ፓስት ሲያጋጥም የነበረው አለመረጋጋት ወደ ሰላም መመለሱን ተናሯል፡፡
ኮማንድ ፖስቱ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ በቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ በኢሉአባቦራና ቡኖ በደሌ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺና ማኦኮሞ የታጠቁ ኃይሎች ጥፋት ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ገልጿል።
ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑት እነዚህ ሀይሎች እጃቸውን በሠላም እንዲሰጡ የደረገ መሆኑንና፥ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ደግሞ የገቡበት ገብቶ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አስረድቷል።
የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ ባንኮች፣ የንግድ ድርጅቶችና ሌሎችም ሙሉ በሙሉ ሥራ መጀመራቸውን አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡም ያለምንም ሥጋት በአካባቢው በመንቀሳቀስ የዕለት ተዕለት ተግባሩን እያከናወነ መሆኑን አመልክቷል፡፡
በቁጥጥር ሥር የዋሉ ህገ-ወጥ ታጣዊዎችንና የያዟቸውን የጦር መሣሪያዎች፣ ገንዘብና ሌሎችንም የጥፋት ግብዓቶች በጥቂት ቀናት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡
ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ሠላም ለመመለስ ባደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ድጋፍ የማይተካ ሚና እንደተጫወተ ጠቅሶ ይህ እገዛ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቋል፡፡ዘገባዉ የኢዜአ ነዉ፡፡