loading
በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ከሌቫንቴ የሚያርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ከሌቫንቴ የሚያርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የስፔን ኮፓ ድል ሬይ (የንጉስ ዋንጫ) የመጨረሻ 16ቱ ቡድኖች የመልስ ግጥሚያቸውን ትናንት አድርገዋል ዛሬም ይከናወናሉ፡፡

ትናንት ከሜዳው ውጭ የተጫወተው ሪያል ማሪድ በሌጋኜስ የ1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፤ በአጠቃላይ ውጤት ግን የዋና ከተማው ቡድን 3 ለ 1 በመርታት ወደ ተከታዩ ዙር ተሻግሯል፡፡

በዋንዳ ሜትሮ ፖሊታኖ ዥሮናን ያስተናገደው አትሌቲኮ ማድሪድ 3 ለ 3 አቻ ተለያይቷል፤ ኒኮላ ካሊኒች፣ አንሄል ኮሪያ እና አንቱዋን ግሪዝማን የአትሌቲኮን እንዲሁም ፈርናንዴዝ፣ ስቱዋኒ እና ጋርሲያ የእንግዳውን ቡድን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ በዚህም በድምር ውጤት 4  ለ 4 በመለያየታቸው ዥሮና ከሜዳው ውጭ በርካታ ግቦችን በማስቆጠሩ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

ሲቪያ በአትሌቲኮ ቢልባዎ በሜዳው የ1 ለ 0 ሽንፈት ቢገጥመውም በደርሶ መልስ 3 ለ 2 ውጤት 8ቱን ቡድኖች ተዋህዷል፡፡

ከትናንት በስቲያ ቫሌንሲያ እና ሄታፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ ሶስት ግጥሚያዎች ሲከናወኑ ባለፈው ሳምንት ወደ ስፔን ምስራቅ ዳርቻ ቫሌንሲያ አቅንቶ በሌቫንቴ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ የተመለሰው የካታላኑ ባርሴሎና ኑካምፕ ላይ ምሽት 5፡30 ላይ የመልሱን ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡

የባለፈው ዓመት የዋንጫው አሸናፊ ባርሳ ወደ ሩብ ፍፃሜው ለመቀላቀል የግድ ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ሪያል ሶሴዳድ ከ ሪያል ቤቲስ እንዲሁም ኢስፓኞል ከ ቪያሪያል በምሽቱ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ሪያል ሶሴዳድና ኢስፓኞል በመጀመሪያው ዙር ካመዘገቧቸው ውጤቶችና ይህን ግጥያ በሜዳው እንደማድረጋቸው መጠን ወደ ሩብ ፍፃሜው የመሻገር ዕድል አላቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *