loading
በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ 

በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ ።

እነዚሁ 850 ኢትዮጵያውያን በሁለት ዙር ባሳለፍነው ሳምንት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመለሻቹ መካከል 445 ያህል ሰዎች ባሳለፍነው አርብ፣ ቀሪዎቹ 405 ደግሞ እሁድ እለት ወደሀገራቸው የገቡ ናቸው።

ከስደት ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በራሳቸው ፈቃድ ሲሆን ሳዑዲ አረቢያ የገቡትም ቀይ ባህርን አቋርጠው በህገ-ወጥ መንገድ እንደነበር ተነግሯል።

ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው የገቡት የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጅዳ በሚገኘው ቆንስላ ጽ/ቤት በኩል ከሳኡዲ አረቢያ መንግስትና ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር ባደረጉት ትብብር ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያዊያኑ ከስደት ተመላሾች  ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ዳይሬክተር ጄኔራሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳኡዲ አረቢያና በሌሎች አገራት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ዜጎች በሰላም ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *