loading
በሳምንቱ የተከናወኑ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ስኬታማ ውጤት እንዳስመዘገቡ  ተገለጸ

በሃገሪቱ ባሳለፍነው ሳምንት በተከናወኑት የውጭ ጉዳይ ስራዎች የተሳካ አፈጻጸም እንደነበራት ሚኒስቴሩ አስታወቀ።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የተካነወኑ ጉዳዮችን  በማስመልከት የሚኒሰቴር መስሪያቤቱ  ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው  በሰጡት  ጋዜዊ መገልጫ ላይ እንደተናገሩት  በቅርቡ የደረሰውን የአውሮፕላን አደጋ ተካትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር  በመሆን  ሀገር ውስጥ  ላሉ ኢንባሲዎች እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች በማነጋገር  መረጃ የመስጠት ሚናውን  መወጣቱን ገልፀዋል፡፡

አቶ ነቢያት የፈረንሳዩ  ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ውደ ኢትዮጵያ መምጣት አስታውሰው  ለኢትዮጵያ በርካታ ጉዳዮችን ጥቀም እንዳስገኘ  እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ ስምምነቶች መደረጋቸውንም እንስተዎል፡፡

በሌላ በኩልም በተገባደደው  ሳምንት ኢትዮ- ቱኒዚያ  የሚኒስትሮች የ ጋራ ኮሚሽን ስብሰባ  በትላንትናው ዕለት በቱኒዚያ መካሄዱን አንስተው  ሁለቱ ሀገሮች በቱሪዚም በባህል እና በኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎች  በርካታ ስራዎችን  በጋራ ለመስራት  መስማማታቸውን   ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው ጨምረውም  ከመጋቢት 4 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 8 ቀን ድረስ  ባሉት ቀናት በአራት  ዙር በተለያዩ አረብ ሀገራት ያለስራ ፍቃድ ሲኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ  የማድረጉ  ጥረት በሳምንቱ ከተከናወኑ አበይት ክስተቶች መካከል እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *