loading
በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መልካም ውጤት አስመዝገበዋል

በለንደን ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች አትሌቶች ኬንያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሁነዋል፡፡

በወንዶች ኢሉይድ ኪፕቾጌ በ2፡02፡37 ጊዜ ቀዳሚ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሞስነት ገረመው በ2፡02፡55 ሁለተኛ፣ ሙሌ ዋሲሁን በ2፡03፡16 ሶስተኛ እና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ቶላ ሹራ ኪጣታ አራተኛ እና ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በሴቶች ብሪጊድ ኮስጌይ በ2፡18፡20 ስታሸንፍ፤ ሌላኛዋ ኬንያዊት ቪቪያን ቼሮይት በ2፡20፡14 ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሮዛ ደረጀ በ2፡20፡51 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሰዋል፡፡   

ከፍተኛ ትግል በነበረበት በሀምቡርግ ማራቶን በወንዶች ታዱ አባተ በ2፡08፡26 1ኛ፣ አየለ አብሽሮ በ2፡08፡27 2ኛ እና ዩጋንዳዊው ስቴፈን ኪፕሮቲች በ2፡0፡32 3ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሲሆኑ በሴቶች ድባቤ ኩማ በ2፡24፡42 ቀዳሚ ስትሆን ኬንያዊቷ ማጋዳላይሜ ማሳይ እና ታንዛናዊቷ ፋይሉና ማታንጋ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ኬንያዊያን ወንድ አትሌቶች ባለድል በሆኑበት ውድድር በሴቶች ሻሾ እንሰርሙ አሸንፋለች፡፡

በጣሊያን ፓዶቫ ማራቶን በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አያንቱ አበራ ደምሴ በ2፡29፡30 ድል አሳክታለች፡፡

በሞሮኮ ዜጎታ የ10 ኪ.ሜ ጠጄ መኮነን በ35፡51 አሸንፋለች፡፡ በኒው ዮርክ Healthy Kidney የ10km ውድድር ሰንበሬ ተፈሪ በ30:59 ጊዜ ቀዳሚ ሁና አጠናቅቃለች፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *