በሱሉልታ ከተማ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
በሱሉልታ ከተማ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
በሱሉልታ ከተማ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ 6 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከማተዋ ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ዲርባባ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አደጋው የደረሰው የከተማ አውቶብስ ከጫንጮ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ሱሉልታ ከተማ ሲደርስ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ከሚጓዝ ተሳቢ የጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
በአደጋው የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ በ4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በ10 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ለህክምና የተላኩ ሲሆን ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሱሉልታ ጤና ጣቢያ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአደጋው የህዝብ ማመላለሻ የከተማ አውቶብሱ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ገልጸዋል።