በሞቃዲሾ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 በሞቃዲሾ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በአደጋው ከሞቱት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም ተነግሯል፡፡ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ቡድን ጥቃቱን ስለማድረሱ ሃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን ጥቃቱም
ለጉዞ በአየር መንገዱ የተገኙ ነጭ ባለስልጣናትን ዒላማ ያደረገ ነበር ብሏል፡፡
በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ፍንዳታው በተከሰተበት አካባቢ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሸከርካሪዎች ሲያልፉ ማየታቸውን ተናግረው የጥቃቱ ዒላማ እነሱ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተ.መ.ድ ልዑክ በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ሰራተኞቹ እንዳልነበሩ በመግለጫው አመላክቷል፡፡
የሞቃዲሾ ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው በወቅቱ በስፍራው እንደነበሩ ገልጸው ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው መናገራቸውን አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል፡፡
አደጋው የደረሰው በሶማሊያ የፖለቲካ እና የፀጥታ አለመረጋጋት በተባባሰበት ወቅት መሆኑ ለስሟ መልካም አለመሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራል፡፡
በሶማሊያ በተፈጠረ ፖለቲካዊ አለመግባባት ሳቢያ ሊካሄድ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወሳል፡፡