loading
በማድሪድ የ10 ኪ.ሜ ሩጫ ጥሩነሽ ዲባባ ሶስተኛ ወጥታለች

በማድሪድ የ10 ኪ.ሜ ሩጫ ጥሩነሽ ዲባባ ሶስተኛ ወጥታለች

በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ዋዜማ በስፔን መዲና ማድሪድ ላይ 54ኛው የሳን ሲልቬስትሬ ቫዬካና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በሴቶች የተካሄደውን ውድድር ብሪጊድ ኮስጌይ እና ሄለን ኦቢሪ በ30 ደቂቃ ውስጥ በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ሲያሸንፉ፤ ጥሩነሽ ዲባባ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

ኮስጌይ ውድድሩን በ29፡54 ቀዳሚ ስትሆን ከዚህ ቀደም በ10 ኪ.ሜ የጎዳናም ሆነ የትራክ ላይ ውድድሮች ተሳትፋ የማታውቀው ሄለን ኦቢሪ በ29፡59 ሁለተኛ በመሆን ስትጨርስ፣ የአለም እና ኦሌምፒክ ጥምር ድል ባለቤቷ ጥሩነሽ ዲባባ በ30፡40 ጊዜ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

በወንዶች የተካሄደውን ውድድር ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በውድድሩ ታሪክ ክብረወሰን የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ድል አድርጓል፤ የገባበት ሰዓት ደግሞ 26፡41 ሁኖ ተመዝግቧል፡፡ በ2006 ኢሉይድ ኪፕቾጌ ካስመዘገበው ጊዜ በ13 ሰከንድ ያህል የተሻሻለ ሁኗል፡፡

ኢትዮጵያዊው አባዲ ሀዲስ በ26፡54 ጊዜ ሁለተኛ እንዲሁም ሌላኛው ዩጋንዳዊ አትሌት ማንዴ ቡሼንዲች በ27፡24 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡

የሳን ሲልቬስትሪ ቫዬካና የ10 ኪ.ሜ ውድድር በIAAF የብር ደረጃ የተሰጠው ሲሆን ከ1964 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *