loading
በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ

በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ

ኪዳል ከተባለችው የማሊ ክልል በ200 ኪሎሜትር  ርቀት ላይ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ካምፕ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በጥቃቱ 10 የቻድ ወታደሮች ህይዎታቸው ሲያልፍ ሌሎች 25 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

የመንግታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በረቀቀ መንገድ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብለዋል፡፡

አልቃኢዳ ኢን ኢስላሚክ መግረብ የተሰኘው ቡድን ጥቃቱን ያደረስኩት እኔ ነኝ በማለት  ሀላፊነቱን መውሰዱን የሞሪታኒያው አል አክባር የዜና ወኪል በዘገባው አስነብቧል፡፡

ቡድኑ ይህን ጥቃት ለማድረስ ምክንያት የሆነውም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለጉብኝት ቻድ መግባታቸው መሆኑን ቡድኑ ይፋ አድርጓል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማሊ 1 ሺህ 200 የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ያሰማራ ሲሆን ሀገሪቱ ለሰላም አስከባሪ ሀይሎች እጅግ አደገኛ ከሚባሉት ሀገራ በቀዳሚነት ትገኛለች፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ማሊ ውስጥ አልቃኢዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስን  ጨምሮ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በስፋት የሚገኙ መሆናቸው ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *