loading
በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ ታራሚዎች ላይ አሁንም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነዉ ተባለ፡፡

በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ ታራሚዎች ላይ አሁንም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነዉ ተባለ፡፡
ይህ የተባለዉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአማራ ክልል ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና እንባ ጠባቂ ተቋም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን በጎበኘበት ወቅት ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ ባገኙት መረጃ ታራሚዎችን ያለበቂ ምክንያት ከአንድ ማረሚያ ቤት ወደ ሌላ ከማዘዋወር ባለፈ አሁንም በክልሉ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች ዘንድ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡
በተመሳሳይም ወጣት ጥፋተኞችን በትምህርትና በስነምግባር አንፆ ወደ ቤተሰቦቻቸው ከመመለስ ይልቅ ለረጅም ጊዜ ከአዋቂ ታራሚዎች ጋር ተቀላቅለው እንዲታረሙ በመደረጉ ወጣቶች ለከፋ እንግልትና ለስነ-ልቦና ጉዳት እየተጋለጡ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ቡድን ተገንዝቧል፡፡
ተጠርጣሪ ወንጀለኛች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ሳይዳኙ ለብዙ ወራቶች በደረቅ ጣቢያ አንዲቆዩ መደረጉ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው እየተጣሰ እደሆነም የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መረዳት ችሏል፡፡
የሁለቱ ተቋማት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ከተቋቋሙበት ጊዜ ጀምሮ የህግ ማዕቀፍ፣ የአደረጃጀትና የመዋቅር ችግሮች እንደነበሩባቸው የቋሚ ኮሚቴ ቡድኑ ተረድቶ አሁን ላይ ተቋሞቹ በውስጣዊና በውጫዊ ችግሮች ምክንያት ለዜጎች ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ ነው ማለት እንደማይቻል አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ የጂኤጂ ምደባ፣ የግብዓት አቅርቦት አና የአመራር አቅም ውስንነትቶች እአንዳሉ የገለጹት የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአቤቱታ አቀራረብና በሰነድ ምርመራ ሂደት ላይም በርካታ ችግሮች እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ከተወካዮች ምክርቤት  እንዳገኘነዉ መረጃ የእንባ ጠባቂ ተቋም ባህርዳር ቅርንጫፍ ሰራተኞች በበኩላቸው መስሪያ ቤቱ በመንግስት ደረጃ ትኩረት የተነፈገው እንደሆነ ገልጸው የህግና የመዋቅር ማሻሻያ፣ እንደሁም የደመወዝና የጥቅማጥቅም ማስተካከያ ተደርጎ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ካልተቻለ ተቋሙ መታጠፍ ወይም መፍረስ አለበት ሲሉ ሃሳብ አንስተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *