loading
በህንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከመቶ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች ሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ፡፡

በህንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከመቶ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች ሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የህንዷ ኬራላ ግዛት ህንድን በክፍለ ዘመኑ ካጋጠማት አስከፊውን የጎርፍ አደጋ አስተናግዳለች፡፡
የግዛቷ ባለስልጣናት እንደተናገሩት በአደጋው ሳቢያ 164 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪም ቁጥራቸው ወደ 23 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪዎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡
ባለስልጣናቱ ነዋሪዎቹ በፍጥነት የአደጋውን አካባቢ ለቀው እንዲወጡም በጥብቅ አሳስበዋል፡፡
በሀገሪቱ አሁንም ከባድ ዝናብ የሚጠበቅ በመሆኑ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኝ አየር መንገድ ለመጭዎቹ አስር ቀናት ዝግ ሆኖ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
የግዛቷን ነዋሪዎች ከሞት ለመታደግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር ሰራዊት አባላትና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሄሊኮፕተሮችና በህይዎት አድን ጀልባዎች የታገዘ የነፍስ ማዳን ስራ እየሰሩ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *