loading
በሁለት ቀናት ዉስጥ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 5.2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ተያዘ

በሁለት ቀናት ዉስጥ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 5.2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ተያዘ

ነገሩ እንዲህ ነዉ  በሁለት ግለሰቦች በሁለት ቀን የተፈጠረዉ ድርጊት

ታህሳስ 21/2011 ዓ.ም መነሻዉን ዱባይ ያደረገዉ  አቶ ቴዎድሮስ በርሄ ከቀኑ 4 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች በተደረገ አካላዊ ፍተሻ መንገደኛዉ በለበሰዉ የዉስጥ ሱሪ 3.2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም ታህሳስ 22/2011 ዓ.ም ከዱባይ የተነሳዉ ተጓዥ አቶ ሰላሙ ደረጀም ቦሌ አለም አቀፍ ኤሪፖርት ከሌሊቱ 4 ሰዓት ሲደርስ በጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ አካላዊ ፍተሻ ግለሰቡ 2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
በሁለት ቀናት የተያዘዉ አጠቃላይ የብር ጌጣጌጥ 5.2 ኪ.ግ ሲሆን ግምታዊ ዋጋዉም 312 ሺ ብር መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፣ የኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ላይ የሚያስከትለዉን ጉዳት በመገንዘብ ኮንትሮባንዲስቶች ከዚህ ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ እና በቅ/ፅ/ቤቱ ያለዉ ክትትል እና ቁጥጥርም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡

መረጃዉን ያገኘነዉ ከገቢዎች ሚኒስቴር ነዉ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *