ቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቻይና መልስ አሰብን ጎብኝተዋል፡፡
አርትስ 30/12/2010
ሰሞኑን በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ቤጂንግ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አሰብ ገብተዋል።
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰብ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰብ ወደብንና ከአሰብ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን 71 ኪሎ ሜትር መንገድ የጎበኙ ሲሆን፥ መንገዱ አገልግሎት ለመስጠት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገምግመዋል።
የአሰብ ወደብ የተወሰኑ የማስተካከያ ስራዎች ከተከናወኑለት በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላም የምጽዋን ወደብ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ የንግድ መርከብ ከረጅም ጊዜ በኋላ በዛሬው ዕለት ምጽዋ ወደብ ላይ መልህቋን ትጥላለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው። FBC