ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ወደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት እንደማይመለስ አስታወቀ፡፡
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ወደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት እንደማይመለስ አስታወቀ፡፡
ኃይሌ ይህንን ያለው ከአርትስ ቴሌቪዥን ጋር ብቻ ባደረገው ቆይታ ነው፡፡
በዚህ ሰሞን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች እና በሌሎች፤ ሻለቃ ኃይሌ ወደ ቀድሞው ኃላፊነቱ እንደሚመለስ ግፊት እየተደረገበት ነው የሚለው መረጃ የብዙሃኑን ቀልብ ስቧል፡፡
አረትስም እውን መረጃው እውነታ አለው ወይ ብሎ ጠይቋል፤ አርሱም መጠየቁን ነገር ግን እንደማይመስ አስረግጧል፤ ምክንያቱም እንድመለሰ ሁኜ አልወጣሁም ሲል አስረድቷል፡፡
ከፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቱም በስሜታዊነት እንዳለቀቀ፤ በእርሱ የተመራው አመራርም ወደ ፌዴሬሽኑ ሲመጡ ብዙ የተበላሹ ነገሮች መኖራቸውንና ያንንም ለማፅዳት በሚሞክርበት ወቅት አንዳንድ ሰዎች ደስተኛ እንዳልነበሩ አስታውቋል፡፡
እጅ ሰጥቷል የሚባለውን ነገር ግን እንደማይቀበለው ተናግሯል፡፡
እኔን ወደ ኃላፊነት ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ ከኃላፊነት እንድነሳ ምክንያት የሆነው ነገር እንዲጣራ እንደሚፈልግ ኃይሌ ገብረስላሴ አሳስቧል፡፡
በቀጣይም ፌዴሬሽኑን ማጎለበት ላይ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግሮ፤ አሁንም ቢሆን አትሌቲክሱን መምራት ያለበት አትሌቱ ነው አሊያ ግን እርሱ ሊመለስ (ሊመጣብኝ) ይችላል ሲል ገልጧል፡፡